Sunday, September 22, 2024
spot_img

በሆሮ ጉድሩ ዞን ከስብሰባ ሲመለሱ የነበሩ ስምንት ሚሊሺያዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ታጣቂዎች በትላንትናው ዕለት በሰነዘሩት ጥቃት፤ ስምንት ሚሊሺያዎች እና አንድ አርሶ አደር መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ከጥቃቱ የተረፉ ሚሊሺያዎች ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ሁለት ሚሊሺያዎች በተጨማሪነት ለቆሰሉበት ለዚህ ጥቃት የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች “ኦነግ ሸኔ”ን ተጠያቂ አድርገዋል ነው የተባለው።

የትላንቱ ጥቃት የተፈጸመው የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ አስተዳደር በጠራው ስብሰባ ላይ ተሳትፈው እየተመለሱ ባሉ ሚሊሺያዎች ላይ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

በስብሰባው ላይ ከአጋምሳ እና ሰምቦ ጨፌ የሄዱ 17 ሚሊሺያዎች መገኘታቸውን በቦታው የነበሩ አንድ ሚሊሺያ ተናግረዋል።

ተሰብሳቢዎቹ ተኩስ የተከፈተባቸው አመሻሽ 12 ሰዓት ገደማ ከወረዳው መሰብሰቢያ አዳራሽ ወጥተው በእግራቸው ወደ መንደራቸው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት መሆኑን ሚሊሺያው አብራርተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img