Saturday, November 23, 2024
spot_img

የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ቴልአቪቭ ኤምባሲ ልትከፍት ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― ከባለፈው ዓመት አንስቶ ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ የተስማማችው የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ፣ በእስራኤል ከተማ ቴልአቪቭ ኤምባሲ ልትከፍት መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት በእስራኤል የምትክፍተው ኤምባሲ መቀመጫው በእየሩሳሌም ሳይሆን፣ በቴል አቪዝ መሆኑ መነጋገሪያ መሆኑን የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ አመልክቷል፡፡

በእስራኤል የኤምሬትስ አምባሳደር መሐመድ አል ሃጃ እየተሰናዳ በሚገኘው የኤምባሲ መክፈቻ ሥነ ሥርዐት፣ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡

ከረዥም ጊዜያት በኋላ በአሜሪካ አሸማጋይነት ወደ መደበኛ ግንኑነት የተመለሱት ሁለቱ አገራት፣ የዛሬ ዓመት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ‹‹ሐሎ እንደምን አለህ›› ከተባባሉበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡

ይኸው የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት እና የእስራኤል ግንኙነት በወቅቱ በበርካታ አገራት በጎ አስተያየት የተሰጠው ቢሆንም፣ ፍልስጤም፣ ኢራንና ቱርክ ግን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን እርምጃ ‹‹ክህደት›› ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img