Monday, October 14, 2024
spot_img

ሲሚንቶ ከዛሬ ጀምሮ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ ተወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― የሲሚንቶ ግብይትን የሚወስነው እና በንግድና ኢንዱስትሪ ተግባራዊ ሲሆን የቆየው መመሪያ መሻሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህንኑ በሚኒስቴሩ የንግድና እቃዎች ጥናትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰ ጊዜ ሲሚንቶ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ የተወሰነው ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራዎች ስለሚቀንስና ከሱ ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ስለሚቅንስ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንዳይኖር መንግስት ከውጪ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁና ፋብሪካዎች ምርታቸው እንዲጨምር በመደረጉ መሆኑን አቶ ካሳሁን አብራርተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img