Monday, October 14, 2024
spot_img

የሕወሓት ኃይሎች ግዛት ለማስመልስ እናደርገዋለን ያሉትን ጦርነት መጀመራቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሐምሌ 6፣ 2013 ― የሕወሃት ኃይሎች በትግራይ ከነበረው ጦርነት በፊት የነበሩ ግዛቶችን በሙሉ ለማስመለስ እናካሄደዋለን ያሉትን ጦርነት በአሁኑ ወቅት ወደ ደቡብ ክፍል መቀጠላቸውን ሬውተርስ፣ ቢቢሲ እና አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ይዘዋቸው የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ሬውተርስ የሕወሓት ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ የሕወሃት ኃይሎች ከመቐለ በስተደቡብ በኩል 170 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ኮረም ከተማ መቆጣጠራቸው ተነግሯል፡፡

ቢቢሲ የወጡ ሪፖርቶች አመልከተዋል ብሎ እንደዘገበው ደግሞ ሕወሓት በደቡባዊ ትግራይ ዋነኛዋ ከተማ የሆነችውና ከኮረም 20 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኘውን አላማጣንም ለመቆጣጠር እየገፉ ይገኛሉ ሲል አስነብቧል፡፡

በተጨማሪም የዜና ተቋሙ ሁለት ሥማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአላማጣ ነዋሪዎች የሕወሃት ኃይሎች ከምሽት አምስት ሰዓት ጀምሮ የአላማጣ ከተማን መቆጣጠራቸውን ነግረውኛል ብሏል፡፡

የዓይን እማኞቹ እንደሚሉት ከከተማ ወጣ ብሎ በሶስት የገጠር መንደሮችም ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መስማታቸውን አስረድተዋል ነው የተባለው፡፡

አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ደግሞ የሕወሃት መሪዎች ከተሞቹን መቆጣጠራቸውን ነግረውኛል ሲል ዘግቧል፡፡

መንግሥት እነዚህ ከተሞች በሕወሃት ኃይሎች ስር ቁጥጥር ስለመሆናቸው የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።

ሬውተርስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ለሆኑት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የኮረም ከተማ በማን ቁጥጥር ስር ነው ያለችው በሚል ጥያቄ አቅርቤላቸው በቀጥታ ባይመልሱም ‹‹የተኩስ አቁም አውጀናል›› የሚል የጽሑፍ መልዕከት ሰደውልኛል ብሏል፡፡

ከሰሞኑ ሕወሓት ምዕራብ ትግራይ የሚላቸውን ግዛቶች በተመለከተ የአማራ ክልል ቀደም ሲል የተወሰዱብኝ አካባቢዎች ናቸው በማለት የሚነሳው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለውና የአማራ አካባቢዎች ናቸው የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የአማራ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ‹‹ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋዕትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን›› በማለት አስፍሮ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img