Monday, October 14, 2024
spot_img

ደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንትዋን እስር ተከትሎ የተነሳን ሁከት ለመቆጣጠር ሠራዊቷን አሰማራች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሐምሌ 6፣ 2013 ― የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ እስርን ተከትሎ በሃገሪቱ ለተፈጠረው አመጽ ምላሽ ለመስጠት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ‹‹ህዝቡ አመጹን እንዲቃወሙ›› ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ሳምንት ዙማ እጃቸው ለፖሊስ ከሰጡ በኋላ ሱቆች ተዘርፈው፣ ሕንፃዎችም ተቃጥለው ቢያንስ ስድስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ወደ 500 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በጋውቴንግ ግዛት እና በዙማ የትውልድ ስፍራ በክዋዙሉ-ናታል ወታደሮች መሠማራታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ዙማ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ሰርተውታል በተባለው የሙስና ክስ ላይ ምርመራ ላይ መገኘት ባለመቻላቸው በእስር እንዲቀጡ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል፡፡

የሙስና ክሱን ያስተባበሉት የ79 ዓመቱ ዙማ የ15 ወር እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ቅጣቱ በሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እንዲሰረዝ ወይም እንዲቀነስ ለማድረግ ተስፋ የተደረገ ቢሆንምየህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን የመሳካት ዕድሉ አነስተኛ ነው፡፡

ራማፎሳ ትላንት ሰኞ ዕለት በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ‹‹በዴሞክራሲያችን ታሪክ ውስጥ እምብዛም የማይታይ›› ያሉትን የህዝብ አመጽ ድርጊቶችን እንደሚያወግዙ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ የተቀሰቀሰው አመጽ በመዲናዋ ጆሃንስበርግ ተዘምቶ ዘራፊዎች ከሱቆች ቴሌቪዥኖችን፣ ማይክሮዌቮችን እና ልብሶችን ሲወስዱ ታይተዋል፡፡

ራማፎሳም ‹‹አሁን እያየነው ያለነው የወንጀል ድርጊቶች ናቸው። ቡድኖች ብጥብጥን እንደ መሸፈኛ አድርገው ይዘርፋሉ›› ብለዋል፡፡

‹‹በኩዌዙሉ ናታል እና በጋውቴንግ የተመለከትነውን ሁከትና ውድመት ሊያረጋግጥ የሚችል ቅሬታ ወይም የፖለቲካ ምክንያት›› እነደሌለም ገልጸዋል፡፡

እሑድ ዕለት ዱላ፣ የጎልፍ መምቻ እና አጠና የያዙ ሰልፈኞች በጆሃንስበርግ የንግድ ስፍራሰዎች ሲንቀሳቀሱ ተስተውሏል፡፡

በደቡብ አፍሪካ በተነሳወ በሁከቱ ምክንያት የኮቪድ-19 የክትባት ፕሮግራም ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩም እየተነገረ ይገኛል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img