Tuesday, October 8, 2024
spot_img

በአፋር ክልል በመሠረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ ሰበብ ማኅበራዊ ቀውስ እየተከሰተ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 5፣ 2013 ― በአፋር ክልል ውስጥ በሚገኙ በርካታ ዞኖች መሠረታዊ የባንክ እና ሌሎች አገልግሎቶች መቋረጥ ጋር በተገናኘ ማኅበራዊ ቀውስ መከሰቱ እየተነገረ ይገኛል፡፡

በክልሉ በተለይ ኪልባቲ ረሱ ዞን የስልክ፣ የባንክ፣ የኃይል አገልግሎቶች ከተቋረጡ 8 ወራት መቆጠራቸው የተነገረ ሲሆን፣ በሌሎችም አካባቢዎች የባንክ አገልግሎት ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የመሠረታዊ አገልግሎት መቋረጡ የተከሰተው ድንበር ከሚያዋስነው በትግራይ ክልል ካለው ጦርነት ጋር የተገናኘ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በክልሉ ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት የባንክ አገልግሎት ለማግኘት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ እንዳለባቸው የተነገረ ሲሆን፣ ይኸው ባስከተለው ችግር ጥሬ ገንዘብ ማግኘት አዳጋች በመሆኑም በርካቶች መቸገራቸው ተሰምቷል፡፡

ክልሉን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው ዘገባ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልልን ለቅቆ ሲወጣ የተቋረጡት የኢንተርኔት፣ የባንክና የመብራት አገልግሎቶች በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን ሥር ባሉ ስምንት ወረዳዎች በተመሳሳይ ወቅት መቋረጡ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ነዋሪዎቹ በወቅቱ እንደጠቆሙት ወረዳዎቹ መሠረታዊ አገልግሎቶቹን በሚሰጡት ተቋማት የሰሜን ሪጅን ስር የተካተቱ በመሆናቸውና በወረዳዎቹ ከጦርነት ሸሽተው የመጡ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በመኖራቸው ነው አገልግሎታቸው የተቋረጠው።

የወረዳዎቹ ነዋሪዎች መሠረታዊ አግልግሎቶቹን ለማግኘት ሰመራ ከተማ ድረስ ለመሄድ ቢገደዱም አገልግሎቶቹን ለማግኘት ክልከላ እንደተደረገባቸው ጠቁመው ነበር፡፡ የባንክ ሒሳባቸው በወረዳዎቹ ይገኙ በነበሩ 8 የንግድ ባንኮች የተከፈቱ በመሆናቸው፣ ሰመራ በሚገኙ ባንኮች አገልግሎት ለማግኘት ጥያቄ ሲያቀርቡ የባንክ ሒሳባቸው እንደተዘገባቸውና አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችሉ ከባንኮቹ ኃላፊዎች ተነግሮናል ብለዋል፡፡

በዚህ እቀባ ሰበብ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ የጠቆሙት የወረዳው ነዋሪዎችና በአካባቢው የሚገኙት የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ከመሠረታዊ አገልግሎቶች በተጨማሪ፣ ከሠመራ የምግብ አቅርቦቶችን ገዝተው ሲመለሱ የጅቡቲ የንግድ መስመር ወደ ትግራይ የሚታጠፍበት ክልል ጋር በሚዋሰንበት ሰርዶ በምትባል ከተማ አዲስ ኬላ ባቋቋመው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደሚንገላቱም አስረድተዋል። ነዋሪዎቹ ችግሩን ለአካባቢው ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ቢየሳውቁም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img