Sunday, October 6, 2024
spot_img

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ የተቋረጠው የስልክ እና የመብራት አገልግሎት በአፋጣኝ መፍትሔ እንደሚበጅለት መናገራቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተቋረጠው የስልክ እና የመብራት አገልግሎት በአፋጣኝ መፍትሔ እንደሚበጅለት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ጋር በወቅታዊው የክልሉ ሁኔታ ላይ በተነጋገሩበት ወቅት መግለጻቸውን የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

በዚሁ ውይይት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት መንግሥት በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦት እንዲደርስ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ማረጋገጣቸውና ይኸው ጉዳይ በዋና ጸሐፊው በበጎ መወሰዱ ነው የተነገረው፡፡

በተጨማሪም በውይይቱ ላይ አንቶንዮ ጉቴሬዝ መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦትን ለማፋጠን እና የእርሻ ወቅትን ታሳቢ በማድረግ የተኩስ አቁም ማወጁ እውቅና መስጠታቸው ተገልጧል፡፡

አሁን ለተኩስ አቁሙ እውቅና የሰጡት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት አንቶንዮ ጉቴሬዝ፣ ከቀናት በፊት መንግሥት የተኩስ ባወጀበት ወቅት፣ መብራት እና ሌሎች አገልግሎቶችን እያቋረጡ የተኩስ አቁም የለም ሲሉ ቅሬታ አሰምተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img