Sunday, October 13, 2024
spot_img

ከሳውዲ አረቢያ ከ21 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 2፣ 2013 ― ባለፈው ሰሞን በጀመረው ዜጎችን የመመለስ ሂደት እስካሁን ድረስ 21 ሺሕ 1 መቶ 82 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ መመለስ እንደተቻለ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል።

ዜጎችን ወደ አገራቸው በማስመለስ ሂደት 99 በረራዎች የተደረጉ ሲሆን፣ ከተመላሽ ዜጎች መካከል 3ሺህ 8መቶ 6 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 1ሺህ 1መቶ 60ዎቹ ደግሞ ህፃናት ናቸው ተብሏል።

በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ላይ እየደረሰ ያለውን እስርና እንግልት ተከትሎ ኢትዮጵያ ዜጎቿን የማስወጣት ስራ መጀመሯ ይታወሳል፡፡ በየቀኑም በርካታ ዜጎች ወደ አገራቸው እየገቡ እንደሆነ አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ በአጭር ጊዜ ውስጥም በሳውዲ የሚገኙ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ የማስወጣት ስራው ይጠናቀቃል ማታቸውን የኢትዮ ኤፍ ኤም ዘገባ ያመለክታል፡፡ በሳዑዲ አረቢያ ከ 40 ሺህ በላይ ዜጎች በችግር ላይ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወቃል።

እነዚህ ዜጎች ለብዙ እንግልትና ስቃይ የተዳረጉ ሲሆን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በትናንቱ የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ፤ የህዳሴ ግድቡ በድህነታችን ምክንያት በስደት ባሉበት አገር፣ በባዶ እግራቸው እየተባረሩ ላሉም ዜጎች መፍትሔ ያመጣል ማለታቸው ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img