Sunday, October 13, 2024
spot_img

የሕወሃት ኃይሎች በደቡባዊ ትግራይ ወስደውታል በተባለ ርምጃ አባሎቻቸው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ፓርቲዎች ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 2፣ 2013 ― መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ መከላከያ ሰራዊትን ከትግራይ ማስወጣቱን መግለጹን ተከትሎ ክልሉን የተረከበው፣ ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል በማለት የሚጠራው ሕወሓት የሚመራው ኃይል የንጹኃን ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ኢ ሰብዓዊ ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡

የፓርቲው ጽሕፈት ቤት እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ከበደ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል መውጣቱን ተከትሎ አሁን ላይ በሕወሓት ኃይል ቁጥጥር ስር በደቡባዊ ትግራይ በሚገኘው የራያ አዘቦ አካባቢ የሚገኙ የራያ ተወላጆች ለበርካታ ችግሮች መጋለጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እስካሁን 50 የሚደርሱ ንጹኃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ከ30 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የወጣበትን ምክንያት የሚደግፉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄም እንዲሁ፣ በክልሉ 22 አባሎቻቸው በሕወሓት ኃይል ተገድለዋል ብለዋል።

አባሎቹ የተገደሉት አንዳንዶቹ በሚስቶቻቸው፣ ለሎቹ ደግሞ በልጆቻቸው ፊት መሆኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡ እንደ ዶክተር አረጋዊ ገለጻ፣ አባሎቻቸው የተገደሉት በአቃቂ ሁኔታ ነው፡፡

አሰቃቂ ነው የተባለውን ጥቃት ፈጽሟል በሚል የተወነጀለው ከሕወሓት ወገን የተሰጠ ምለሽ አለመኖሩን መረጃው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img