Sunday, September 22, 2024
spot_img

በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ከነበሩ ተማሪዎች የተወሰኑት በእግራቸው እየወጡ ይገኛሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 2፣ 2013 ― በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በእግራቸው አካባቢውን እየለቀቁ ወደ ወሎና አፋር አካባቢዎች መግባታቸው ተነግሯል፡፡

በክልሉ መቀመጫ መቐለ ከተማ በሚገኘው አይደር ሆስፒታል የተግባር ትምህርት ላይ የነበሩና ዘንድሮ የምርቃት ሥነ ሥርዐታቸውን ሲጠባባቁ የነበሩ የሕክምና ተማሪዎችን ጨምሮ ከሠላሳ በላይ ተማሪዎች በተሸከርካሪና በእግራቸው አቆራርጠው ደሴ ከተማ መግባታቸውን የአሜሪካ ድምፅ ከራሳቸው ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

እነዚሁ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው የወጡት ትምህርታቸውን በተረጋጋ መንፈስ ለማስቀጠል የሚያስችል የሥነ ልቦና ዝግጅትና ምቹ ሁኔታ ስሌለለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ከቀናት በፊት በይፋዊ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት ተማሪዎቹ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዐመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ናቸው ማለቱ ይታወቃል፡፡

ተማሪዎቹ እንደሚሉት ግን በትምህርት ቤት ግቢዎቻቸው ውስጥ የመንግሥት ደጋፊና ተቃዋሚ የሚል ፍረጃ በመፈጠሩ በተማሪው መካከል ውጥረት መኖሩ አካባቢውን ለቀው ለመውጣት አስገድዷቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ተማሪዎቹ ከትምህርት ግቢያች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ ላደረገልን ድጋፍና ተቆርቋሪነት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውም ተመላክቷል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት አካባቢዊውን መልቀቅ ተከትሎ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች በእግራቸው መውጣት መጀመራቸው እየተሰማ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ከትግራይ ወደ አፋር ሰመራ የዘለቁ ተማሪዎች መኖራቸውን የአሜረሪካ ድምጽ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ከክልሉ ተመልሰናል ያሉትን ተማሪዎች አስመልክቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር አመራሮች የሰጡት ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img