Sunday, October 13, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ለሌሎች ተጠሪ የሆነ ደካማ መንግሥት የመፍጠር ትግል እየተደረገ መሆኑን የገዢው ፓርቲ ኃላፊው ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 1፣ 2013 ― በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሌሎች ተጠሪ የሆነ ደካማ መንግስት የመፍጠር ትግል እየተደረገ መሆኑን የገዢው ፓርቲ ብልጽግና በላሥልጣን የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ ገልጸዋል፡፡

አቶ ታዬ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ማስታወሻ ሕወሃት በጥቅምት ወር መጨረሻ በቢትዮጵያ መካላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን እንዲሁም በማይካድራ ‹‹የዘር ማጥፋት›› መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡

ይህንኑ ተከትምሎም የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሳይወድ በግድ በትግራይ ላይ የህግ ማስከበር ዘመቻ አውጇል›› ያሉት ታዬ፣ ‹‹ወድያዉ በሰብዓዊ መብቶችና በረሐብ ስም ብዙዎች የኢትዮጵያን መከላከያ መክሰስ›› መጀመሩን አስረድተዋል፡፡

ታዬ አክለውም፣ ‹‹ክልሉ እንዲበለፅግና ሰብዓዊ መብት እንዲከበር አሜሪካና አጋሮቿ የኢትዮጵያ መከላከያ ትግራይን ይለቅ ዘንድ መክረዋል›› ያሉ ሲሆን፣ ‹‹መንግስት ግራና ቀኙን ከገመገመ በኋላ ደግሞ የትግራይ ህዝብ የጥሞና ግዜ አግኝቶ ትርፍና ኪሳራውን እንዲያሰላ ለማስቻል የኢትዮጵያ መከላከያ ትግራይን በውሳኔ መልቀቁንም ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በክልሉ ‹‹የተባለዉ ጥጋብና ሰብዓዊነት›› ግን ይበልጥ መራቁንና ጁንታው ሲሉ የሚጠሩት የሕወሃት ቡድን፣ ‹‹ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ይገኛል›› ሲሉ አመልክተዋል፡፡ አቶ ታዬ ለዚህ ማሳያ ብለው ‹‹በእንደርታና በራያ “ለውጡን ደገፋችሁ” በሚል ብዙ ሰዎች ሲገደሉ አብዘኛው ታፍኖ›› መወሰዱነ አመልክተዋል፡፡

በሽሬም በተመሳሳይ ‹‹ከ300 የሚበልጡ የኤርትራ ስደተኞች›› ታርደዋል ያሉ ሲሆን፣ የበርካቶች ቤት ከመዘረፉም በላይ ተቃጥሏል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካ መንግሥት ከትላናት በስትያ ያወጣውና አቶ ታዬ አስገሚ ያሉትን መግለጫ አስመልክቶም ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ‹‹የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ባወጣው በጁንታው ከተጨፈጨፉት ንፁሃን ይልቅ ጁንታዉ ያፈረሰው የተከዜ ድልድይ እንዳሳዘነዉ ገልጿል›› ሲሉ ተችተውታል፡፡

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አክሎም ‹‹በትግራይ ጉዳይ የስምምነት ተኩስ አቁም፣ ሁሉን ያካተተ የሽግግር ውይይትና ያልተገደበ የድጋፍ ፍሰት እንዲኖር ጠይቋል፣ የውጭና የውስጥ የኢትዮጵያ ድንበርም በህሀ መንግስቱ መሠረት ይቆይ ዘንድ አሳስቧል›› ያሉት አቶ ታዬ፣ ጥያቄው የሕወሀት የጦር አዣዥ ናቸው የሚባሉት ጀነራል ጻድቃን ከሰሞኑ ለሚዲያ ከተናገሩት ጋር ‹‹ቃል በቃል ይመሳሰላል›› ብለዋል፡፡

አቶ ታዬ ደናደኣ በማሳረጊያቸው ‹‹አሁን ብዥታዉ ጠርቷል›› በማለት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ አጀንዳ የማን እንደሆነ ለይቷል፤ በኢትዮጵያ ለሌሎች ተጠሪ የሆነ ደካማ መንግስት የመፍጠር ትግል መሆኑን በግልፅ ታይቷል›› ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ሆኖም ግን ‹‹ምርጫው በሰላም ተጠናቆ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጀመሩ ግን እጅግ ብዙ የባዳና የባንዳ ፋይሎችን ይዘጋል›› ሲሉ ደምድመዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img