Sunday, October 6, 2024
spot_img

አሜሪካ የትግራይ ጦርነት ተፋላሚዎች በአስቸኳይ ሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሳሰበች

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 30፣ 2013 ― የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው አንቶንዮ ብሊንክን በትላንትናው እለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስልክ ደውለው በትግራይ ሙሉ የተኩስ አቁም እንዲደረግ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

የሁለቱን አገራት ባለሥልጣናት የስልክ ውይይት ዝርዝር ይፋ ያደረጉት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፣ ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የፌዴራል መንግሥት ያወጀው የተኩስ አቁም መሬት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዲኖርበት ብሊንክን መናገራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ሌላ በክልሉ የሚደረገው የሰብአዊ አቅርቦት ያለ ገደብ እንዲደርስ መፍቀድ አስፈላጊ መሆኑን ያመለከቱት ብሊንክን፣ ባለፈው ሳምንት በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዲተገበር የተጠየቀውን የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ልዩ ኃይል ክልሉን ለቀው የመውጣት ጉዳይ አንዲያስፈጽሙ እንዲሁም አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲደረጉም ጠይቀዋል፡፡

ብሊንክን የሚወክሏት አሜሪካ፣ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን ካሳወቀበት ያለፈው ሳምንት መጀመያ በኋላ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መነጋገሯን ይፋ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img