Sunday, October 6, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩን ሂውማን ራይትስ ዎች አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 29፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ለአዲስ ግጭት ዝግጅት መኖሩን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች በትዊተር ገጹ ላይ ጠቁሟል።

ድርጅቱ ዛሬ በድረ ገጹ ላይ በአጭሩ ይፋ ያደረገው መረጃ ትግራይ ውስጥ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ወደ ጎን ብለው ለአዲስ ግጭት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ይገልጻል።

ሂውማን ራይትስ ዎች አክሎም በዚህ መሀልም በግጭት ምክንያት በክልሉ በርካቶች ተፈናቅለው ለረሀብ መጋለጣቸውንም ጠቅሷል።

ዋና መቀመጫው አዲስ አበባ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ይህን ድርጊት ማውገዝ እና የተጠናከረውን በደል ሊያስቆም ይገባው ነበርም ብሏል። ዝምታው እና ምንም ርምጃ አለመውሰዱ እንደሚያሳስብም አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ በትግራይ የሚገኙ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ የእንግሊዙ ‘ዘ ጋርዲያ’ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ የሕወሓት ኃይሎች በብዙ መኪኖች ተጭነው ወደ ምዕራብ አቅጣጫ አምርተዋል።

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር በዛሬው እለት “የአማራ ክልልን ከማንኛውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል” ሲሉ ተናግረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img