Sunday, October 13, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ የሚሰማራው የውጭ ኩባንያዎች ጥምረት ኃላፊ ሾመ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 29፣ 2013 ― በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ አሸንፎ ከመንግሥት ጋር ውል የተፈራረመውና ስድስት ኩባንያዎች የተጣመሩበት ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ (ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ)፤ አንዋር ሱሳ የተባሉ ግለሰብን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙ ተነግሯል፡፡

ኃላፊው ሳፋሪኮም፣ ሲዲሲ ግሩፕ፣ ቮዳኮም፣ ሱሚቶሞ እና ዲኤፍሲ የተባሉት በዓለም ዙሪያ በቴሌኮም ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች በጋራ 850 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ያደረጉበትና በኢትዮጵያ በመቋቋም ላይ የሚገኘውን የቴሌኮም ኩባንያን ይመራሉ።

አንዋር ተጠሪነታቸው ለኩባንያው ቦርድና መሠረቱን ኬንያ ላደረገው ሳፋሪኮም እንደሚሆን ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ (ጂፒኢ) ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ከሰኔ 24፣ 2013 ጀምሮ ለአዲሱ የቴሌኮም ኩባንያ በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት የተሰየሙት አንዋር ሱሳ ግሪካዊ ሲሆኑ ለቴሌኮሙ ዘርፍ አመራር አዲስ አለመሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

እንደ መግለጫው ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ አገልግሎት ለሚሰጠው ጥምረት በኃላፊነት የተሾሙት አንዋር በዲሞክራቲክ ኮንጎ ቆይታቸው ቮዳኮም በአገሪቱ እንደ አውሮፓውያኑ 2020 ላይ 500 ሚሊዮን ዶላር የአገልግሎት ገቢ እንዲያገኝ ያስቻለ አመራር ሰጥተዋል።

በግሪክ አሜሪካን ኮሌጅ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁት ኃላፊው፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ካናዳ ከሚገኘው ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ ማግኘታቸውን መግለጫው ያትታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img