Sunday, October 13, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሹፌር መንቀሳቀሳቸው ወደ ፊት በሕግ ሊታገድ እንደሚችል ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 28፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሹፌር መንቀሳቀሳቸው ወደፊት በሕግ ሊታገድ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሮችም ሆነ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ለመኪኖቻቸው ሹፌሮች ከመቅጠር ይልቅ ራሳቸው ሲያሽከረክሩ ማየት እንደሚፈልጉ የተናገሩት ዐቅላይ ሚኒስትሩ፣ ራሳቸውም መኪና ማሽከርከር የሚያዘወትሩት በምሳሌነት ለማስተማር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ሆኖም ብዙም ለውጥ ባመታየቱ የባለስልጣናት በሹፌር መንቀሳቀስ ወደ ፊት በሕግ ሊታገድ የሚችል መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተደጋጋሚ ከውጭ አገራት የሚመጡ እንግዶቻቸውን ራሳቸው መኪና እያሽከረከሩ ሲያስጎበኙ ይስተዋላል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img