Sunday, November 24, 2024
spot_img

የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የሚያዙበት የአገሪቱ ጦር በትግራይ ጦርነት መሳተፉን ኮነነ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 28፣ 2013 ― የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚው የኤርትራ ነጻነት ግንባር ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የሚያዙበት ያገሪቱ ጦር በትግራይ ጦርነት መሳተፉን ኮንኖ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ግንባሩ ስምንት ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ጦርነት ‹‹አምባገነን›› ሲል በጠራቸውው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ትእዛዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ጋር ተሰልፏል ያለው የኤርትራ ጦር ጣልቃ ገብነት ማድረጉን እንዲሁም ተሳትፎው በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የፖለቲካ እና የደኅንነት ሁኔታ ላይ ጥላ የሚያጠላ ነው ብሎታል፡፡

የአገሪቱ ጦር በትግራይ ጦርነት ለመሳተፉ ብቸኛው ተጠያቂ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ናቸው ያለው ግንባሩ፣ የጦሩ ተሳትፎ የኤርትራን ሕዝብ እንደማይወክልም ገልጧል፡፡

የኤርትራ ነጻነት ግንባር አክሎም ወንድም ባለው የትግራይ ሕዝብ ላይ ደርሷል ያለውን ግፍ አውግዟል፡፡

በተጨማሪም ግንባሩ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ደርሷል ያለውን ያነሳ ሲሆን፣ ለጥፋቱም የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮችን ወንጅሏል፡፡

የኤርትራ ነጻነት ግንባር በመግለጫው በትግራይ ጦርነት ተፋላሚ ኃይሎች ችግሩን በንግግር እንዲፈቱት የጠየቀ ሲሆን፣ የተኩስ አቁም መታወጁንም በበጎ አንስቶታል፡፡

በፈረንጆቹ በ1950ዎቹ በግብጽ ካይሮ መመስረቱ የሚነገርለት የኤርትራ ነጻነት ግንባር (ተጋደሎ ሓርነት ኤርትራ)፣ ዋና መቀመጫውን በሱዳን ካርቱም አድርጎ የሚንቀሳቀስ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img