Sunday, October 13, 2024
spot_img

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተያዘው ዓመት የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደሚጠበቅ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 28፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት በፓርላማ ቀርበው በተያዘው ዓመት የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ዓመቱ መልካም ዝናብ የነበረበትና የተሻለ የእርሻ ወቅት መሆኑ ምርታማነትን ጨምሯል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተትሩ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በበጋ ስንዴ 15 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም በቡና በምርት ብዛትና ወደ ውጪ በመላክ የተሻለ ገቢ አስገኝቷል ያሉ ሲሆን፣ ማዕድን ከቡና ቀጥሎ የተሻለ የወጪ ንግድ ገቢ የተመዘገበበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ውጪ ሃገራት የሚላኩ ምርትች በ18 በመቶ ጭማሪ መታየቱን፣ እንዲሁም የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ1 ሺህ ዶላር በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡

ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በውጭ 100 ቢሊዮን፣ በሃገር ውስጥ ደግሞ ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img