Monday, November 25, 2024
spot_img

ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰኑ 8 የአፋር ክልል ወረዳዎች መሠረታዊ አገልገሎቶች በመቋረጣቸው ነዋሪዎች መቸገራቸው ተጠቆመ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 26፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልልን ለቅቆ ሲወጣ የተቋረጡት የኢንተርኔት፣ የባንክና የመብራት አገልግሎቶች በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን ሥር ባሉ ስምንት ወረዳዎች በተመሳሳይ ወቅት መቋረጣቸው ታውቋል።

እነዚህ ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰኑ ወረዳዎች በተቋረጡት መሠረታዊ አገልግሎቶች ሰበብ፣ ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ መቸገራቸውን ለአምባ ዲጂታል ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚጠቁሙት ወረዳዎቹ መሠረታዊ አገልግሎቶቹን በሚሰጡት ተቋማት የሰሜን ሪጅን ስር የተካተቱ በመሆናቸውና በወረዳዎቹ ከጦርነት ሸሽተው የመጡ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በመኖራቸው ነው አገልግሎታቸው የተቋረጠው።

የወረዳዎቹ ነዋሪዎች መሠረታዊ አግልግሎቶቹን ለማግኘት ሰመራ ከተማ ድረስ ለመሄድ ቢገደዱም አገልግሎቶቹን ለማግኘት ክልከላ እንደተደረገባቸው ጠቁመዋል። የባንክ ሒሳባቸው በወረዳዎቹ ይገኙ በነበሩ 8 የንግድ ባንኮች የተከፈቱ በመሆናቸው፣ ሰመራ በሚገኙ ባንኮች አገልግሎት ለማግኘት ጥያቄ ሲያቀርቡ የባንክ ሒሳባቸው እንደተዘገባቸውና አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችሉ ከባንኮቹ ኃላፊዎች ተነግሯቸዋል።

በዚህ እቀባ ሰበብ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ የጠቆሙት የወረዳው ነዋሪዎችና በአካባቢው የሚገኙት የትግራይ ክልል ተፈናቆይች ከመሠረታዊ አገልግሎቶች በተጨማሪ፣ ከሠመራ የምግብ አቅርቦቶችን ገዝተው ሲመለሱ የጅቡቲ የንግድ መስመር ወደ ትግራይ የሚታጠፍበት ክልል ጋር በሚዋሰንበት ሰርዶ በምትባል ከተማ አዲስ ኬላ ባቋቋመው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደሚንገላቱም አስረድተዋል። ነዋሪዎቹ ችግሩን ለአካባቢው ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ቢየሳውቁም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img