Sunday, October 13, 2024
spot_img

በካናዳ በአዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ያገሬው ቀደምት ነዋሪዎች አስከሬን መገኘቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የንግሥት ቪክቶሪያ እና የንግሥት ኤልሳቤጥ ሐውልት ፈረሰ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 26፣ 2013 ― በካናዳ አዳሪ ትምሕርት ቤት ውስጥ ያገሬው ሰቀደምት ነዋሪዎች አስከሬን መገኘቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ፣ የእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የንግሥት ኤልሳቤጥ ሐውልት ፈርሷል፡፡

በየዓመቱ በሚከበረው የካናዳዊያን ምሥረታ ቀን የፈረሱተ ሐውልቶቹ፣ ከዚህ ቀደም በድምቀት ይከበረ የነበረውን በዐል ሲያደበዝዘው፣ በርካታ አወራጃዎችም በዐሉን እንዲሰረዝ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

በ1867 ከቅኝ ግዛት የተላቀቀችው ካናዳ፣ በአገሯ የሚገኙ የንግሥት ቪክቶሪያ እና የንግሥት ኤልሳቤጥ መፍረሱን ተከትሎ የቀድሞ ቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ድርርቱን እንደኮነነች የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በካናዳ በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን 150 ሺሕ ያህል ያገሬው መሠረት ያላቸው ልጆች ከሌሎች ጋር እንዲዋሃዱ ከቤተሰቦቻቸው ተወስደው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ ይደረጉ እንደነበርና ከነዚህ መካከል 6 ሺሕ የሚሆኑት መሞታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

በካናዳ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከሐውልቶቹ መፍረስ በተጨማሪ በርካታ የካቶሊክ ቤተክርስትያናት ጥቃት እንደደረሰባቸው ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img