Monday, September 23, 2024
spot_img

ሲፒጄ ባለፉት ቀናት የታሠሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 26፣ 2013 ― ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ባለፉት ቀናት በሁለት ሚዲያዎች የሚሰሩ 15 የሚዲያ ባለሞያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በመግለጽ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳ እንዲለቃቸው ጠይቋል፡፡

ሲፒጄ በመግለጫው ሰኔ 23 እኩለ ቀን ላይ ፖሊስ በአዲስ አበባ የሚገኘው አውሎ ሚዲያ ማዕከል በኃይል መግባቱን እና 12 የማዕከሉን ሠራተኞች ሰለማሰሩ ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁ ሰምቻለሁ ብሏል።

ከቀናት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሚዲያ ባለሞያዎቹ እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን፣ እንዲሁም ለመታሰራቸው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንዳልተነገራቸው ሲፒጄ ጨምሮ አስነብቧል።

በተመሳሳይ ኢትዮ ፎረም በተባለ ዩቲዩብ ቻናል አማካይነት ዜና እና ትንታኔ ያቀርቡ የነበሩ አበበ ባዩ እና ያየሰው ሽመልስ የተባሉ ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጿል።

ሲፒጄ የሚዲያ ባለሞያዎቹን እስር በተመለከተ በትላንትው እለት ባወጣው መግለጫ መንግሥት በቅርቡ ያሰራቸውን ጋዜጠኞችን እና የሚዲያ ባለሞያዎችን በአስቸኳይ እንዲለቅ እና በሞያው የተሰማሩ ላይ ያሚያደርሰውን ጫና እንዲያቆም ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጄላ ኩይንታል ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የኢትዮ ፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ማዕከል ባልደረቦችን በአስቸኳይ መልቀቅ አለበት›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ፣ የአውሎ ሚድያ እንዲሁም የኢትዮ ፎረም ባልደረቦች የሆኑ የሚድያ ባለሞያዎች በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንደዋሉ መረጃ ደርሶኛል ያለ ሲሆን፣ ማኅበሩ ባለሞያዎቹ ስለተያዙበት አካሄድ እና አሁን ስላሉበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግኩ እገኛለሁ ብሏል።

ባለፉት ቀናት በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጋዜጠኞች መካከል የኢትዮ ፎረሞቹ አበበ ባዩ፣ ያየሰው ሽመልስ እንዲሁ የአውሎ ሚዲያው በቃሉ አላምረው ይገኙበታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img