Update: የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የአውሎ ሚድያ እንዲሁም የኢትዮ ፎረም ባልደረቦች የሆኑ የሚድያ ባለሙያዎች በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንደዋሉ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።
ማኅበሩ በጋዜጠኞቹ መያዝ ዙርያ በቂ መረጃ ማግኘት ባይችልም፣ የሚመለከተው የመንግስት አካል በህግ ከለላ ስር የሚገኙ እነዚህ የሙያ አጋሮቻችን በተቻለ መጠን በፍጥነት ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ የህግ ድጋፍ የማግኘት እንዲሁም የመጎብኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል።
የጋዜጠኞች በብዛት መታሰር እንዲሁም በመያዛቸው ዙርያ መረጃ በተገቢው ፍጥነት ይፋ አለመደረግ በሙያው ውስጥ ያሉ ተቋማት ፣ ባለሙያዎችና የሚድያ ድርጅቶች ላይ ያልተገባ ስሜት ይፈጥራል ያለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር፣ ይህን ለማስወገድ የሚመለከተው አካል በቀናነት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።