Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ እና የደኅንነት ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በተኩስ አቁሙ ላይ ቅሬታቸውን አሰሙ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 25፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት የውጭ እና የደኅንነት ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ከሰሞኑ በመንግሥት የታወጀው የተኩስ አቁም ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ቦሬል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ማስታወሻ፣ የተኩስ አቁም ማለት አንድን ክልል ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ማድረግ፣ አሊያም መሠረተ ልማቶችን ማውደም አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዐይነተኛ የተኩስ አቁም የሚባለው የሰብአዊነት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካላት እንዲደርሳቸው የተቻለውን ሁሉ ማድረግ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው፣ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የሕይወት አድን ሥራ ነው ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ መንግሥት በትግራይ ክልል የመኸር ወቅት እስኪያልፍ የተኩስ አቁም ማወጁን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ሆኖም የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የረድኤት ተቋማት በክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጣቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዋንኛው የሰብአዊ አቅርቦት መስመር ነው የሚባለው የተከዜ ድልድይ፣ በትላንትናው እለት መፍረሱ የተነገረ ሲሆን፣ ለድልድዩ መፍረስ የፌዴራል መንግሥት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሃትን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በበኩሉ፣ ድልድዩን የአማራ ልዩ ኃይል አፍርሶታል የሚል መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡

ሆኖም በመንግሥታቱ ድርጅት በድልድዩ መፍረሰ ሥሙ የተጠቀሰው የአማራ ልዩ ኃይልን የሚያዝበት የአማራ ክልል የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img