Monday, September 23, 2024
spot_img

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በጸጥታ ኃይሎች ታፍኖ መወሰዱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 25፣ 2013 ― በበይነ መረብ የሚሠራጨው ኢትዮ ፎረም ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው እለት የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በለበሱና ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ መሰወዱን ኢትዮ ፎረም አሳውቋል፡፡

እንደ የሚሠራበት ኢትዮ ፎረም ዘገባ ጋዜጠኛው ታፍኖ የተወሰደው ‹‹ባለፈው ዓመት ተከሶበት በነበረውና የዋስ መብቱ ተከብሮለት በተለቀቀበት ‹የሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት› ክስ ላይ በዛሬው ዕለት ጠዋት 4 ላይ በቀጠሮ መሰረት ለመቅረብ ከቤቱ ወጥቶ ወደ ልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መኪናውን እያሽከረከረ እየሄደ ሳለ›› ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የትና በምን ሁኔታ እንዳለ የሚሠራበት ኢትዮ ፎረም ለማወቅ ጥረት ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ሌላኛው የዚሁ የበይነ መረብ ሚዲያ ባልደረባ የሆነውና ከሳምንት በፊት ድብደባ የተፈፀመበት አበበ ባዩ፣ ትላንት ምሽቱን 3፡20 አካባቢ በድጋሚ የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በለበሱና ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ መወሰዱ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img