Sunday, September 22, 2024
spot_img

ዴቪድ ሺንን ጨምሮ አምስት የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደሮች ሁሉም አካላት የተኩስ አቁም ጥሪውን እንዲቀበሉ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― በቀደመው ጊዜ አገራቸው አሜሪካቸው ወክለው በኢትዮጵያ ያገለገሉ አምስት አምባሳደሮች፣ በትግራይ ጦርነት ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም ተፋላሚ አካላት በኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበውን የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲቀበሉ በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ ቪኪ ሀድልስተን፣ ፓትሪሽያ ሃስላች፣ ኦሬሊያ ብራዚይል እና ቲቦር ናዥን የያዘው ቡድን በጻፈው ደብዳቤ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ሰቆቃ ለማስቆም ሊባክን የማይገባው እድል ነው ያሉትን በመንግሥት የታወጀውን የተኩስ አቁም ጥሪ፣ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ሊቀበሉት የሚገባው ነው ብለዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በደብዳቤያቸው ተፋላሚ አካላት የተኩስ አቁሙን በክልሉ በቋሚነት ሰላም ለማስፈን እንዲሁም በትግራይ ክልል መጻኢ ይዞታ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ይጠቀሙበት ብለዋል፡፡ አክለውም ሰላም እንዲሰፍን ከተደረገ በኋላ በጦርነቱ የተጠቃው አካባቢ መልሶ እንዲቋቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻዎች ውይይት እንዲያካሄዱም ጠይቀዋል፡፡

በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎችም የሰብአዊ አቅርቦት እንዲዳረስ ክፍት ይደረግ ያሉት የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደሮች፣ ጦርነቱ ባለበት አካባቢ የሚገኙ የውጭ ኃይሎችም ለቅቀው እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በደብዳቤያቸው ማሳረጊያ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኮሚሽን ጋር በክልሉ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ ለማካሄድ ያቀዱትን ምርመራ እንዲያፋጥኑት ጠይቀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img