Saturday, October 12, 2024
spot_img

በሳዑዲ ኢትዮጵያውን ላይ የሚደረገው እንግልት ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ ጫና ለመፍጠር መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 23፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትላንት ማምሻውን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፖርክ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በተገኙበትና በምርጫው ወቅት መገናኛ ብዙኃን በነበራቸው አስተዋጽኦ ዙርያ ምሥጋና ባቀረቡበት መድረክ በሳዑዲ ኢትዮጵያውን ላይ የሚደረገው እንግልት ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ ጫና ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ በጸጥታ አካት አፈሳ እና እንግልት ሲደረግባቸው መቆየቱ መነገሩ ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንትናው መድረክ ላይ ይህንኑ የስደተኛ ኢትዮጵያውኑንን እንግልት እና አፈሳ ነው ከሕዳሴ ግድብ ጋር ጫና ለመፍጠር የሚደረግ ነበር ያሉት፡፡

ስደተኞቹን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ልኡክ በመስደድ መነጋገሩም አይዘነጋም፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አንስቶ ዜጎችን እየመለሰ እንደሚገኝ የተናገረ ሲሆን፣ አሁን ወደ አገር ቤት እየተመለሱ የሚገኙት ረዥም ጊዜ በአገሪቱ የቆዩት ናቸው ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img