Monday, November 25, 2024
spot_img

የተመድ የሕፃናት መርጃ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች ቢሮው ገብተው የሳተላይት ቁሳቁሶችን አውድመውብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች በትላናትናው እለት ቢሯቸው በኃይል ገብተው የሳተላይት ቁሳቁሶችን ማውደሙን አሳውቋል፡፡

ይህንኑ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያነሱት የድርጅቱ ዳይሬክተር ሄንሬታ ፎሬ፣ ድርጊቱ ተገቢ አይደለም በሚል አውግዘውታል፡፡

ዩኒሴፍ በአሁኑ ወቅት ለረሐብ ተጋላጭ የሆኑ 140 ሺሕ ያህል ሕጻናትን ለመርዳት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ ኢላማ መደረግ እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡

ጨምረውም በትግራይ ክልል የጦርነቱ ተፋላሚ የሆኑ ሁሉም አካላት የጦርነት ሕጎችች እንዲያከብሩና የረድኤት ድርጅቶችንም እንዲከላከሉ ጠይቀዋል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር ሄንሬታ ፎሬ በረድኤት ድርጀቶች ሥራ ጣልቃ መግባት እንደማይኖርባቸው እና የነርሱ ሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና ከለላ መስጠት ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሥማቸው ቁሳቁሶችን በማውደም የተነሳው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ በትላናትናው እለት የትግራይ ክልል መቀመጫ መቀለ ከተማን ለቀው መውጣታቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img