Thursday, October 10, 2024
spot_img

በትግራይ ጦርነት ተሳትፋለች በሚል ሥሟ ተነስቶ የነበረው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ በትግራይ የተኩስ አቁም መደረጉን ደገፈች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― በትግራይ ጦርነት ተሳትፋለች በሚል ሥሟ ተነስቶ የነበረው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በትግራይ ክልል ከትላንት ጀምሮ ተኩስ እንዲቆም መደረጉ አግባብ መሆኑን የሚደግፍ መግለጫ አውጥታለች፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ተኩስ እንዲቆም መደረጉ የሚደገፍ ሐሳብ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረበለትን የተኩስ አቁም ጥያቄ ትላንት ምሽት መቀበሉ የሚታወስ ሲሆን፣ አረብ ኤምሬትን ርምጃው ትክክለኛ መሆኑን ገልጻለች፡፡

አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በደስታ እንደተቀበለችው ገልጻ፤ በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም ፖለቲካዊ መፍትሄ ብቸኛው አማራጭ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ውሳኔው ለችግሮች የፖለቲካ መፍትሄ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑንም አቡዳቢ ገልጻለች፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ስምንት ወራት ባስቆጠረው የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት ተሳትፋለች በሚል በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መነሳቷ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img