Saturday, October 12, 2024
spot_img

የሕወሃት ኃይሎች ‹‹ወራሪ›› ያሉት ኃይል ትግራይን ሙሉ ለሙሉ ለቆ እስከሚወጣ እንደሚፋለሙ አሳወቁ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― በትላንትናው እለት የአገር መከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልል መቀመጫ የመቀለ ከተማን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ዳግም መቀሌን ተቆጣጥሯል የተባለው የሕወሃት ኃይል ‹‹ወራሪ›› ሲል የሚጠራቸው የአገር መከላከያ ሠራዊትና እና ሌሎች ኃይሎች የትግራይን መሬት ሙሉ ለሙሉ ለቀው እስከሚወጡ ድረስ እንደሚፋለም አሳውቋል፡፡

የሕወሃት ኃይሎች ይህን ያሳወቁት የፌዴራል መንግሥት ትግራይን ከመቆጣጠሩ በፊት ያስተዳድር በነበረው የክልሉ መንግሥት ሥም ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

የሕወሃት ኃይሎች የአፍሪካ ታላቁ የጦር መሪ ባት አሉላ አባነጋ በተሰየመው ዘመቻ ድል ማድረጋቸውን ያመለከተው መግለጫው፣ በአሁኑ ወቅት የክል መቀመጫ የመቀሌ ከተማም በቁጥጥራቸው ሥር እንደገባች አውጇል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የሕወሃት ኃይሎች አሸንፈነዋል ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚያዙበት የመከላከያ ሠራዊት ጥፋት ሊያደርስ ሰለሚችል የከተማው ወጣቶች ከጎናቸው እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ሕጋዊ የተባለው ሕወሃት ለሚመራው መንግሥት ሁሉም ዜጎች ተባባሪ እንዲሆኑ ይኸው መግለጫ ጠይቋል፡፡

ሕወሃት አሸንፌዋለሁ ያለው የፌዴራል መንግሥት በትላንትናው እለት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረበውን የተኩስ አቁም ጥያቄ መቀበሉን ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img