Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የቀድሞው የግንቦት ሰባት አመራር መከላከያ ሕወሃቶችን አሳንሶ ተመልክቷል ሲሉ ተቹ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 22፣ 2013 ― የአገር መከላከያ ሠራዊት የሕወሃት ኃይሎችን አሳንሰው እየተናገሩ የሕወሃት ኃይሎች “ሁለት መቶ ሺሕ ሠራዊት” የተማረከ ወይም የተደመሰሰ አድርገው ለኢትዮጵያ ሕዝብ መናገራቸው ስህተት እንደነበር የቀድሞው የግንቦት ሰባት አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ገልጸዋል።

የሕወሃት ኃይሎች መቀሌን ዳግም መቆጣጠራቸውን በጣም ያማል ያለት አቶ ነአምን፣ በመከላከያ በኩል “ይህ ክፉ ቀን” እንዳይመጣ የሚያስፈልገው ዝግጅት፣ ስትራቴጂም ሆነ ብቃት እንዳልነበር ለመታዘብ ይቻል ነበር ሲሉ ነበር ያሉትን ክፍተት አመልክተዋል።

አቶ ነአምን የመንግሥት ሰዎችም ሕወሃት ጥርስ የነቀለበት ነው ያሉትን የሽምቅ ውጊያ ሊገለበጥ የሚችል፣ የሕዝብን ምሬትና ብሶት በመጠቀም መልሶ ሊጠናከር እንደሚችልም ከግምት እንዳላስገቡ መታዘብ ይቻል ነበር ብለዋል።

አቶ ነአምን ዘለቀ የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው የጊዜያዊ አስተዳደርም በሕወሃት ሰላዮችና ከዚያ አመለካከት ያልፀዱ የተሰባሰቡበት ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ነአምን ዘለቀ በቅርብ ጊዜያት የዳያስፖራ ማኅበር ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን መንግሥት አቋም ለማድረስ በሚሠራበት ወቅት ከፊት የተሰለፉ የመንግሥት ደጋፊ እና አጋዥ እንደነበሩ ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img