Saturday, October 12, 2024
spot_img

የአገር መከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን መልቀቁ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 21፣ 2013 ― የአገር መከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልል መቀመጫ የሆነችውንና ባለፉት ሰባት ወራት ተቆጣጥሯት የቆየችውን መቐለ ከተማን ለቆ መውጣቱን የሚያመለከቱ ታማኝ መረጃዎች ወጥተዋል።

መከላከያ መቐለን ለቆ የወጣው የሕወሓት ኃይሎች ወደ ከተማው ለመግባት በመቃረባቸው እንደሆነ ነው የተነገረው። አንድ አንድ ለህወሓት ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች የሕወሓት ኃይሎች የመቐለ ከተማን መቆጣጠራቸውን ቢዘግቡም፣ በመንገግሥትም ሆነ በሀገር መከላከያ በኩል ጉዳዩን አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።

ይህንኑ ተከትሎም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳደር አመራሮች ከተማውን ለቀው መውጣታቸው ማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ በከተማው የሚገኙ የባንክ እና መሰል አገልግሎት መስሪያ ቤቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደተዘጉ ተሰምቷል። ዝርፊያና አለመረጋጋትም በከተማው መኖሩን አንድ አንድ ዘገባዎች በተጨማሪነት ያመለክታሉ።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ የሚተላለፈው ትግራይ ቴሌቪዥን ሥርጭቱ እንዲቋረጥ እንደተደረገም ሌሎች ምንጮች ጠቁመዋል።

ከተማዋ ላይ የሚካሄዱ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን እየተከታተልን ለመዘገብ እንጥራለን።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img