Saturday, October 12, 2024
spot_img

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሜዲትራኒያንን ሲያቋርጡ የነበሩ 178 ስደተኞችን ከመስመጥ መታደጉን የቱኒዚያ ጦር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 21፣ 2013 ― ቱኒዚያ ባህር ኃይል ትላንት እሑድ በሊቢያ በኩል ሜዲትራኒያንን አቋርጠው ወደ አውሮፓ በመሻገር ላይ የነበሩ 178 ስደተኞችን ከመስመጥ መታደጉን አስታውቋል፡፡

ባህር ኃይሉ በደቡባዊ የሃገሪቱ ባህር ዳርቻዎች ባካሄዳቸው ሶስት ዘመቻዎች ስደተኞቹን በህይወት ለመታደግ መቻሉን ነው ያስታወቀው፡፡

ስደተኞቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከግብጽ፣ ከአይቮሪኮስት፣ ከናይጄሪያ፣ ከማሊ እና ከሶሪያ እንዲሁም ከባንግላዴሽ የተነሱ ናቸው፡፡

ዙዋራ ከተሰኘች የሊቢያ የባህር ዳርቻ ከተማ ተነስተው አርብ ሌሊቱን ለቅዳሜ አጥቢያ እጅግ አስቸጋሪውን የባህር ላይ ጉዞ መጀመራቸውም ነው የተነገረው፡፡

የቱኒዚያ ባለስልጣናት ባሳለፍነው ሃሙስ 267 በዋናነት ባንግላዴሻውያን ስደተኞችን መያዛቸውንም ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይ.ኦ.ኤም) ገልጿል፡፡ አይ.ኦ.ኤም ሜዲትራኒያንን አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ ስደተኞች መዳረሻቸው ደቡባዊ ቱኒዚያ የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ሆነዋል ይላል መጠለያዎቹ መሙላት መጀመራቸውንም ጠቁሟል፡፡

በሊቢያ ያለው የከፋ ሁኔታ ስደተኞቹ ባህር እንዲያቋርጡ እያስገደዳቸው እንደሆነም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የስደተኞች ኤጀንሲ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል፡፡

የተመድ ከጥር እስከ ግንቦት በነበሩት 5 ገደማ ወራት ሜድትራኒያንን ለማቋረጥ የሞከሩ የ760 ስደተኞች ህይወት ማለፉንም ገልጿል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img