Saturday, October 12, 2024
spot_img

አሜሪካ የኢራኑን ፕረስ ቲቪ ጨምሮ ኢላማ አድርገውኛል ያለቻቸውን ድረ ገጾች ማገዷ አነጋጋሪ ሆኗል

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 21፣ 2013 ― የአሜሪካ የፍትሕ መምሪያ ጽሕፈት ቤት በኢራን መንግሥት የሚንቀሳቀሰው ፐረስ ቲቪን ጨምሮ 33 ድረ ገጾችን ከባለፈው ሳምንት አንስቶ ማገዷን አሳውቃለች፡፡

የአገሪቱ የፍትሕ መምሪያ ድረ ገጾቹን ለማገዱ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው፣ ድረ ገጾቹ አሜሪካን አስመልክቶ መረጃ የተሳሳተ መረጃ ያዛምታሉ የሚል ነው፡፡

የድረ ገጾችን እግድ ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ እግዱን አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጃ ለማዛባት የምታደርገው ጥረት አንዱ ማሳያ ነው ብሎታል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰዒድ ካቲብዛዴህ የአሜሪካን ተግባር አሳፋሪ ነው ያሉት ሲሆን፣ የባይደን አስተዳደር የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ትራምፕን መንገድ እየተከተለ ስለመሆኑ አመልካች ነው በሚል መግለጻቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት ድረ ገጻቸው የታገደባቸው የኢራኑን ፕረስ ቲቪ እና አል ዓለም የተባለውን ድረ ገጽ ጨምሮ፣ ሁሉም ድረ ገጻቸውን ለመክፈት ሙከራ የሚያደርጉ፣ ድረ ገጹ በአሜሪካ መንግሥት መታገዱን የሚገልጽ ማስታወሻ ሰፍሮ ይታይባቸዋል፡፡

አሜሪካ በድረ ገጾቹ ላይ የፈጸመችው እግድ አገሪቱ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ላይ ያላትን አቋም ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው የተለያዩ አካላት ሐሳባቸውን ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img