Saturday, October 12, 2024
spot_img

ኦነግ ምርጫው ተቀባይነት የለውም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 19፣ 2013 ― የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባሳለፍነው ሰኞ የተካሄደውን አገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን ‹‹በምንም መስፈርት›› ተቀባይነት የሌለው ነው ብሎታል፡፡

ከምርጫ ተሳትፎ ቀድሞ ራሱን ያገለለው ኦነግ፣ በዋናነት በመንግስት መዋቅሮች ምክንያት የሚነሱትን ዓላማዎች እና ግድፈቶች እያወቁ በምርጫው ላይ ጥቂት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን አስታወሷል፡፡

እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው በተመለከቱ ጉዳዮች እና በውጤቱ ላይ በልዩነቶች ላይ ማንኛውንም ሁከት ከማነሳሳት እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ ‹‹በእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ማንኛውንም የሕዝብ አመፅ ማነሳሳት በፖለቲካም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የለውም›› ብሏል፡፡

ኦነግ ይልቁንም ሕዝቦች እና አገሪቷ ገጥሟታል ላለው ቀውስ መፍትሄ የሚፈለግበት ጊዜ አሁን ነው በማለት፣ መፍትሔ እንዲመጣ ‹‹በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማ ውይይት እንዲጀመር መንገዱን ለመክፈት››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመታደግ መንግሥት›› ሲል ለጠራው ‹‹ጊዜያዊ አካል›› እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ‹‹የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሰራዊት እና የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሰላምን በማረጋገጥ የኢፌዴሪ የመታደግ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ እናቀርባለን›› ያለው ኦነግ፣ ‹‹በመላ አገሪቱ የሚካሄዱ ጦርነቶችንና ግጭቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆምና የኤርትራ ወታደሮችና የደህንነት ሰራተኞቻቸው በአፋጣኝ እንዲወጡ›› አሳስቧል፡፡

አክሎም የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ሁሉም የፖለቲካ አካላት ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ለፖለቲካዊ ውይይት መንገድ የሚከፍት የሽግግር ስርዓት ለመዘርጋት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img