Saturday, October 12, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ በነገሌ የአንድ መቶ ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ሕጋዊ አይደለም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ክልል ነገሌ ምርጫ ክልል የጣለውን ክልከላ በመጣስ ተካሄዷል ያለው የአንድ መቶ ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ሕጋዊ አይደለም ሲል አሳውቋል፡፡

ከቦርዱ እውቅና ውጭ በምርጫ ክልሉ ትልቅ ግድፈት መፈጸሙን ያስታወቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ፣ ግድፈቱ የታተመው የምርጫ ክልሉ ድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ በሕግ መሠረት የተመዘገበን የግል ተወዳዳሪ ዕጩን ያላካተተ መሆኑን ተከትሎ ያጋጠመ ነበር ብለዋል፡፡

ግድፈቱን በመረዳት ቦርዱ የነገሌ ምርጫ ክልል በመጀመሪያ ዙር ምርጫ ማድረግ የለበትም በሚል ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

ሆኖም ‹‹ማነንቱ ያልተጠቀሰ የመንግሥት ባለሥልጣን አሊያም የምርጫ ቦርድ አመራር›› መቀጠል አለበት በማለቱ ምክንያት፣ ምርጫው ከ100 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች እንዲቀጥል ተደርጓል ያሉት ብርቱካን፣ ‹‹ሕጋዊ›› አይደለም ያሉትን ተግባር ቦርዱ ለፌደራል ፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገና ጥፋቱ የማን እንደሆነ ተጣርቶ ምን ተጠያቂ እንደሚደረግ በቀጣይ እንደሚለይ ተናግረዋል።

በዚህም በምርጫ ክልሉ አንድ መቶ ምርጫ ጣቢያዎች የተደረገው ምርጫ ውጤቱ ሕጋዊ እንደማይሆንም ነው ያሳወቁት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img