Saturday, October 12, 2024
spot_img

ኢዜማ በምርጫ ወቅት ላቀረበው ቅሬታ ከምርጫ ቦርድ ምላሽ ካላገኘ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 17፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባሰለፍነው ሰኞ ሰኔ 14 ቀን የተደረገውን የ6ኛውን አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ውጤት እስከሚገለጽ እንደሚጠብቅ ቢገልጽም፣ በምርጫ ወቅት በምርጫ ክልሎች ያጋጠሙትን ችግሮች ምርጫ ቦርድ በአጽንኦት ተመልክቶ ውሳኔ የማይሰጥባቸው ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካላት ይዘን እንሄዳለን ብሏል፡፡

የምርጫ 2013 አጠቃላይ የፓርቲውን የምርጫ እንቅስቃሴ የሚያስተባብር የምርጫ ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ኮሚቴ ከአመት በፊት አዋቅሮ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ያስታወሰው ፓርቲው፣ ይህ ኮሚቴ አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ከሚያዘጋጀው የግምገማ አጠቃላይ ሪፖርት፣ በድርጅት በኩል፣ በብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተቋቋመ ቡድንና ከፓርቲው ውጪ በተመረጡ ገለልተኛ አካላት ከሚቀርበው ግምገማ በመነሳት አጠቃላይ ሁኔታውን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img