Saturday, October 12, 2024
spot_img

ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የተጠበቁት ክቡር ገና የብልጽግናን አሸናፊነት አወጁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 17፣ 2013 ― ሰኞ እለት በተካሄደው ምርጫ የወከሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ካሸነፈ የአዲስ አበባ ከንቲባ ይሆናሉ ተብሎ በሥፋት ሲነገርላቸው የሰነበቱት ክቡር ገና፣ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫው አሸናፊ መሆኑን አውጀዋል።

አቶ ክቡር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ ውጤት ከመግለጹ ቀድመው አሸንፏል ላሉት ብልጽግና እና ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልአክት ሰደዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዚህ ምርጫ አሸናፊ ናቸው በማለት ያሞገሱት አቶ ክቡር ገና፣ ኢትዮጵያውያንም ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑላቸው ወስነዋል ነው ያሉት፡፡

ጨምረውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም እንኳ በውጭም ሆነ በውስጥ ጠላቶች ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም፣ ምርጫ እንዲከናወን አድርገዋል በማለት ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ራሳቸው የሚገኙበት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን ሥራ አልሰሩም ያሉ ሲሆን፣ ይህ ለምን ሆነ ብለው ራሳቸውን መጠየቅ፣ መፈተሽ፣ መወያየት እና ለቀጣይ ሥራዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው መክረዋል።

አቶ ክቡር በማሳረጊያቸው ሀገሪቱን ለሚገዛት ብልጽግና ፓርቲ ይድረስ ያሉትን ምክር ለግሰዋል። ከነዚህ መካከል የሰፋውን የኑሮ ልዩነት ማቀራረብ፣ ድህነትን መቀነስ፣ የጤና አገልግሎትን ማስፋት፣ ስራ አጥነት፣ ፍትሕ፣ የተሻለ የንግድ ሥርዐት አመቻችቶ ሥራ ፈጣሪዎችን እና ገቢን ማስፋት እንዲሁም የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት እና አንድነትን ለማምጣት እንዲሠራ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባሳፍነው ሰኞ የተካሄደውን ምርጫ ይፋዊ ውጤት ባይገልጽም፣ በምርጫ ክልሎች የተለጠፉ ውጤቶች ብልጽግና ፓርቲ እየመራ እንደሚገኝ የሚያመለክቱ መሆናቸውን መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img