Saturday, October 12, 2024
spot_img

የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕወሃት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን በጦርነት እየማገደ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 17፣ 2013 ― ሕወሃት ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን በጦርነት እየማገደ እንደሚገኝ የአገር መከላከያ ሠራዊት የ12ኛ መተማ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮለኔል አማረ ሞላ ተናግረዋል፡፡

ሠራዊቱ በምዕራብ ዕዝ የ12ኛ መተማ ክፍለ ጦር በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ደጋ ዓርቢ ማይቅንጥል አካባቢ እየተደረገ ባለው አሰሳና ፍተሻ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ በርካታ ሕፃናትን አስገድዶ እያዋጋ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮለኔል አማረ ሞላ ሕወሃት ሕፃናቱን ‹‹ሳይወዱ በግድ ከቤተሰቦቻቸው በመነጠል ወደ ውጊያ እንዲገቡ በማድረግ፣ ኅብረተሰቡን እንደ መደበቂያ በመጠቀም እና የሐሰት ወሬ በመንዛት›› ማኅበረሰቡ የእለት ከዕለት ኑሮውን እንዳይመራ አድርገውታል ብለዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት በአሰሳና ፍተሻው ወቅት ከሕወሀት አምልጠው እጅ የሰጡ ወጣቶች ሕወሃት ‹‹ከ12 እስከ 15 አመት ያሉ ሕፃናትን ሳይወዱ በግዳቸው በመመልመል እያዋጋቸው መሆኑን መስክረዋል›› ሲልም አስታውቋል፡፡

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች በአገር መከላከያ ሠራዊትና በሕወሃት ኃይል መካከል ከባድ ውጊያ ማገርሸቱ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img