Saturday, October 12, 2024
spot_img

ከመተከል ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ ከ16 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ነበሩበት እየተመለሱ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― ከመተከል ዞን ተፈናቀለው በቻግኒ ከተማ ራንች መጠለያ የነበሩ 16 ሺህ 531 ዜጎች ወደ ድባጢና ቡለን ወረዳዎች እየተመለሱ መሆኑን የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጋራ ግብረ ኃይል ቴክኒክ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቀለሙ ሙሉነህ ተናግረዋል።

ተመላሾቹ በተመረጠላቸው ቦታ ተረጋግተው እንዲኖሩ አስፈላጊው ግብዓትና ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ቀለሙ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ ከድባጢ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 564፣ ከቡለን ተፈናቅለው የነበሩ 4 ሺህ 416 እና ከወንበራ ተፈናቅለው የነበሩ 511 በድምሩ 16 ሺህ 531 ዜጎች ተመልሰዋል።

የወንበራና እና የቡለን ተመላሾች በዶቢ ማዕከል በተዘጋጀላቸው መጠለያ የሚያርፉ ሲሆን የድባጢ ተመላሾች ደግሞ በድባጢ ማዕከል እንደሚሰፍሩ ምክትል ሰብሳቢው ገልጸዋል።

የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ተመላሽ ወገኖችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅቱ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው ዜጎቹን መልሶ በማቋቋም እና ደህንነታቸውን በማስጠበቅ በኩል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለተመላሽ ወገኖች የሚደገረገው ሁሉን ዓቀፍ ድጋፍ በክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ደግሞ በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ ሙንተዚር አልቁረይሽ ናቸው።

በቻግኒ ከተማ ራንች እና አካባቢው ከ50 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደነበሩ እና ከዛሬዎቹ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የማንዱራና የዳንጉር ተፈናቃዮች መመለሳቸውን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያን ዋቤ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img