Friday, October 11, 2024
spot_img

በውስን ምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ እጥረት ከፈጠረው ጫና ውጭ ምርጫው ሰላማዊ እንደነበር የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የሚመራው የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውንና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን የተመለከተ ቀዳሚ የሪፖርት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ምልከታ አድርገናል ያሉት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ምርጫውን ተዘዋውረን በተመለከትንበት፣ የምርጫ ቦርድን ተቋማዊ ጥንካሬ አይተናል፣ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊ የጸጥታ እርምጃ ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል።

ምርጫው ከሞላ ጎደል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው የተካሄደው ያሉም ሲሆን፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በተለይም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከጸጥታ ጋር ተያይዞ ስጋቶች እና በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችን የማዋከብ እና የማንገላታት ችግሮች እንደነበሩ ገልጸዋል።

በምርጫው እለት የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ መንግስት እና የጸጥታ አካላት ስራቸውን በአግባቡ መስራታቸውንም ነው የቁሳቁስ እጥረትና የመራጮች ብዛት በድምጽ አሰጣጡና በቆጠራው ሂደት ላይ ጫናን ፈጥሯል ያሉት ኦባሳንጆ የተናገሩት።

የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት በምርጫው የሚያደርጉትን ተሳትፎ መቀጠልና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማትን፣ በተለይም ለምርጫ ቢርድ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናከሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱ በሚመለከተው አካል ይፋ እስኪሆን ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትእግስት ሊጠባበቁ ይገባልም ነው ኦባሳንጆ ያሉት። ቡድኑ በ5 ክልሎች እና 2 ከተሞች ታዛቢ ልኮ ምርጫውን መታዘቡን አስታውቋል፡፡

ድምጽ ሰጪዎች በምርጫው ደስተኛ መሆናቸውንና የፈለጉትን በነጻነት መምረጣታቸውን ነግረውኛል ያለም ሲሆን የመራጮቹ ትዕግስት አስገራሚ ነበር ማለታቸውንም የዘገበው አል ዓይን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img