Saturday, October 12, 2024
spot_img

ኤርትራ ድንበር ተሻግራ በትግራይ ክልል የራሷ ዜጎች ላይ አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችን መፈጸሟን ለመንግስታቱ ድርጅት የተላከ ሪፖርት አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― በጥቅምት ወር በተቀሰቀሰው የትግራይ ክልሉ የፌዴራል መንግሥቱ እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት ወደ ኢትትጵያ ወታደሮቹን ያስገባው የኤርትራ መንግስት፣ በትግራይ ክልል ተጠልለው በነበሩ ዜጎቹ ላይ ጭምር አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችን መፈጸሙን የሚያመለክት ሪፖርት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደተላከ ተነግሯል፡፡

በኤርትራ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚያዘጋጁት መሐመድ ዐብዱልሰላም ባቢከር በላኩት ሪፖርት፣ በመብቶች ጥሰት ሥሟ የሚነሳው ኤርትራ የምትፈጽማቸው ጥሰቶች መሻሻሉን የሚያመለክት ነገር የለም ብለዋል፡፡

ይባስ ብሎ ድንበር በመሻገር በትግራይ ክልል አሰቃቂ የሚባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሟን አመልክተዋል መባሉንም የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡

ባቢከር እንዳሉት ከሆነ በትግራይ የሚገኙት የአገሪቱ ወታደሮች በንጹሐን ላይ ግድያ፣ በሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር እንዲሁም በትግራይ መሬት ላይ የሚገኙ የራሳቸው አገር ዜጎችን ሰውረዋል፡፡

በተጨማሪም የኤርትራ ወታደሮቸ በትግራይ ክልል ይገኙ የነበሩትና ከ25 ሺሕ በላይ ስደተኞችን የያዙትን ሁለት መጠለያዎችን በማውደም ሥማቸው ተነስቷል፡፡

መሐመድ ዐብዱልሰላም ባቢከር አሁንም ቢሆን የኤርትራ መንግሥት ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ መሬት እንዲያስወጣ ጠይቀዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img