Saturday, October 12, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳግም ወደ አስመራ በረራ ጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረው ወደ አስመራ የሚደረግ በረራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ የሚያደርገው በረራ ከዛሬ ረቡዕ አንስቶ የሚጀምር መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከሃያ ዓመታት በኋላ የጀመረው የዛሬ ሦስት ዓመታት ገደማ ሐምሌ 11፣ 2018 ነበር፡፡

የበረራ አገልግሎቱ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመታት የባላንጣነት ቆይታ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከተፈረመው ‹‹የአስመራ ዲክላሬሽን›› ከተሰኘ ሰነድ በኋላ የቀጠለ ነበር፡፡

በሰነዱ ላይ ከሰፈሩ ጉዳዮች አንዱ በአንቀጽ 3 ላይ የሰፈረውና በሁለቱ ሀገራት መካከል ተቋርጠው የነበሩት የትራንስፖርት፣ የንግድ እና የኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ የሚጠይቀው ክፍል ይገኝበታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img