Saturday, October 12, 2024
spot_img

በትግራይ በገበያ ሥፍራ ተፈጽሟል በተባለ የአውሮፕላን ጥቃት በንጹሐን ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ተምቤን ከመቐለ በስተምዕራብ 20 ኪሎ ሜትር ላይ ቶጎጓ በሚባል ሥፍራ ተፈጽሟል በተባለ የአውሮፓላን ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው ንጹሐን ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

በገበያ ቀን ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በመቐለ አይደር ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ለንጹሐን መጎዳት ሰበብ የሆነው ጥቃት በማን እንደተፈጸመ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ሆነ ሌሎች አካላት ያሉት ነገር የለም፡፡

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ውስጥ በአገር መከላከያ ሠራዊትና በሕወሃት ኃይል መካከል ከባባድ ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው የሕወሀት ኃይል በርካታ የክልሉን ከተሞችን መያዙን የገለጸ ሲሆን፣ ተዋጊዎቹ በአካባቢያቸው ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን የዜና ተቋሙ የዐይን እማኞች ነግረውኛል ብሏል፡፡

የሕወሃት ቡድን ከኤርትራ ድንበር በ45 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ወደምትገኘው አዲግራት ከተማ መግባቱም የተነገረ ሲሆን፣ ትላንት ቀትር ላይ ተመልሶ ወጥቷል፡፡ የሕወሃት ቡድን ይህን ያደረገው የገባበው አላማ አቅርቦት ለመሰብሰብ ነው የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ የሆኑት ኮሎኔል ጌትነት ከባድ ውጊያ እንደነበረ አረጋግጠው፤ የሕወሃት ኃይሎች ከተሞችን፣ የጦር መሳሪያዎችን ወይም ወታደሮችን ማርከናል ያሉትን ሐሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img