አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― የሚኒስትሮች ምክር ቤት “የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ” “የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ” በሚል እንዲሰየም ዛሬ ማጽደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።
አካዳሚው ከስም ለውጥ ጋር የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የአመራር ጥያቄዎችን ለማሟላት የሚያስችል ዐቅም ያላቸውን ልሂቃን የሚያፈራ እና የዕድገት ተኮር አስተሳሰብን የሚያንፀባርቅ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ያለመ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።