አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞንና በቦረናና ጉጂ ዞኖች አባካቢ ሲንቀሳቀሱ በነበሩና በምርጫው ሒደት ላይ መስተጓጎል ሊፈጽሙ በነበሩ 26 የታጠቁ ቡድኖች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ታወቀ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ዕርምጃ የተወሰደባቸው 20 ታጣቂዎች ከጅማ ዞን ናቸው፡፡
የጅማ ዞን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በጎማ 2 የምርጫ ክልል ዕጩ ሆነው የቀረቡበት አካባቢ ነው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘረፍ ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን አመንቴ ነግረውኛል ብሎ ሪፖርተር እንደዘገበው፣ በተለያዩ የኦረሚያ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩና በፓርላማ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች በምርጫው ሒደት ላይ መስተጓጎል ለመፍጠር ሞክረው እንደነበርና ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል።
በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ሥፍራዎች የሚንቀሳቀሰውን የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን እንዲሁም ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወቃል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በምርጫው ሒደት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለመከላከል ቀደም ብሎ የሥጋት ልየታና የመካላከያ ዕቅድ አውጥቶ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ ለፖሊዎችም የምርጫ ሒደትን የተለመከቱ ሥልጠናዎች ሲሰጡ ቆይተዋል።
ሆኖም ምርጫው እንዳይካሔድ አስቀድመው ለማስተጓጎል ሲጥሩ የነበሩ ኃይሎች አሉ ያለው ፖሊስ፣ በእንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ታይተው ዕርምጃ የተወሰደባቸው መኖራቸውን አሳውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ከታጣቂ ቡድኖች መካከል ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ዕጅ የሰጡና የተማረኩ እንደሚገኙም ተነግሯል።