አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት ምርጫ ክልለሎች ማለትም አሶሳ ሁሐ እና አሶሳ መንጌለ የሚባሉ በአጠቃላይ 102 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው እንደተሰረዘ ተነግሯል፡፡
ምርጫው የተሰረዘው በትላትናው ዕለት በተፈጠረው የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት ምክንያት መሆኑን በምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ለማን ዋቤ አድርጎ ዶይቸ ቨለ ዘግቧል፡፡
ኃላፊው በተሰረዙት የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ አሰጣጡ እንደገና ለማካሄድ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ይጠበቃል ብለዋል።
በትላትናው ዕለት ምርጫ በተካሄደባቸዉ በሌሎች 6 ስድስት የምርጫ ክልሎች ሰላማዊ እና በተሟላ መልኩ ምርጫው መካሄዱን የክልልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ተናግረዋል፡፡
አሶሳ ሁሓ እና አሶ መንገሌ የምርጫ ክልሎች በአጠቃላይ በአሶሳ ዞን ከነበሩት 302 የምርጫ ጣቢያዎች በ102ቱ የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል፡፡
በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱት ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ዴሞክራሲያ ፓርቲ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡
የቦሮ ዴሞክራሲቲክ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ትናንት በተደጋጋሚ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታን ሲያቀርብ መቆየቱንና ውሳኔውም ትክክለኛ ፍትሃዊ ነው ብለዋል፡፡
በአሶሳ ዞን ከ360 ሺሕ በላይ ዜጎች ድምፅ ለመስጠት ካርድ መውሰዳቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡