Friday, October 11, 2024
spot_img

ብልጽግና ፓርቲ በአዲስ አበባ እየመራ መሆኑን የምርጫ ውጤቶች አመለከቱ

– የኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በብልጽግና እጩ እየተመሩ ከሚገኙት መካከል ናቸው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 15፣ 2013 ― በትላንትናው እለት በተካሄደው ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ያቀረባቸው ተወዳዳሪዎች አብላጫ ድምጽ በማግኘት እየመሩ እንደሚገኙ የወጡ የምርጫ ውጤቶች አመልክተዋል።

በከተማው እስካሁን ድረስ በወጡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶች መሠረት ከብልጽግና በመቀጠል የባልደራስ ተወካዮች ሲከተሉ፣ ኢዜማ በሦስተኛነት ተቀምጧል።

ከእጩዎች መካከል የኢዜማው ሊቀንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተወዳደሩበት የምርጫ ክልል በብልጽግና እጩ መረታታቸው ተሰምቷል።

የምርጫው ውጤት ሙሉ በሙሉ ይፋ ባይሆንም የኢዜማው እጩ አቶ ዮሐንስ መኮንን ፓርቲያቸው በምርጫው ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥ በመጠቆም፣ “አሸናፊ ባያደርገንም ሐሳባችንን ደግፋችሁ ድምጻችሁን የሰጣችሁን ኢትዮጵያዊያን ከልብ እናመሰግናለን” በማለት ጽፈዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img