Friday, October 11, 2024
spot_img

ፍትሕ መጽሔት የዛሬ ኅትመቱ በመንግሥት ታግዶብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― ሳምንታዊው ፍትሕ መጽሔት በመንግሥት ከማተሚያ ቤት እንደታገደ መጽሔቱ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

የመጽሔቱ እግድ በምን ምክንያት የተደረገ መሆኑን እንደማይታወቅ ያሰፈረው የመጽሔቱ ማስታወሻ፣ የታገደው በየትኛው ማተሚያ ቤት እንደሆነም የጠቀሰው ነገር የለም፡፡

መጽሔቱ በዛሬው እትሙ በሽፋን ገጹ ላይ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ‹‹ለአዲስ አበባ አይሆኑም›› የሚል ርእስ መያዙን በማኅበራዊ ትስስር መድረኮቸ ላይ የተለቀቀው ምስል ያመለክታል፡፡

የዛሬው እትም ታግዶብኛል ያለው ፍትሕ መጽሔት፣ መንግሥትን በሚሸነቁጡ ጽሑፎቹ በሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚመራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img