Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኮሚሽን ለመንግሥት የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ ለመልቀቅ የትግራይ ሁኔታ መሻሻል እስኪያሳይ እንደሚጠብቅ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― በአውሮፓ ኅብረት ስር ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሚያሳልፈው የአውሮፓ ኮሚሽን ሥራ አስፈጻሚ አካል ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ ለመልቀቅ የትግራይ ሁኔታ መሻሻል እስኪያሳይ እንደሚጠብቅ ዴቬክስ የተባለ ድረ ገጽ ተመከልክቼለሁ ያለውን ሰነድ ዋቤ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን በቀጣይ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ትምህርት እና መልካም አስተዳደር ላይ ቅድሚ ሰጥቶ እንደሚሠራ ያመለከተው ዘገባው፣ የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ባሳለፍነው ማክሰኞ በኅብረቱ የበጀት እቅድ ላይ በዝግ በመከረበት ወቅት ለመንግሥት የሚሠጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ የመስጠቱን ነገር ግምት ውስጥ ለማስጋባት ግን በትግራይ ክልል ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ እንደሚጠብቅ ጠቁሟል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ ከሚሰጠው ድጋፍ 40 በመቶው በአየር ንብረት ለውጥ፣ ዘላቂ የኃይል አቀርቦት፣ እና አረንጓዴ ልማት የሚውል ሲሆን፣ ሌላኛው 40 በመቶ ለሰብአዊ ልማት ማለትም ለትምህርት፣ ጤና እና ከስደት ጋር በተገናኘ የሚውል ነው፡፡ 15 በመቶው ለሰላም ግንባታ እና ለአስተዳደር እንዲሁም ቀሪ 5 በመቶ ለሌሎች ድጋፎች ይውላል፡፡

በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ሲያወጣ የሰነበተው የአውሮፓ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትን በቅርብ ቀናት አግኝቶ በመጪ ሰኞ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ እና በሕዳሴ ግድብ ላይ ማነጋጋሩንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img