Friday, October 11, 2024
spot_img

ኢዜማ አባል ያልሆነች ግለሰብ ፎቶ ለቅስቀሳ መጠቀሙ ቅሬታ አሰነሳ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አባል ያልሆኑ ግለሰብ ፎቶ ለቅስቀሳ መጠቀሙ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

ፓርቲው ‹‹አባሉም ሆነ ደጋፊ አይደለሁም›› ያሉትን ዛህራ መሐመድ የተባሉ ግለሰብ፣ በጉራጌ ዞን አንዳንድ ቦታዎች መጠቀሙን ራሳቸው ዛህራ መሐመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀው ነበር፡፡

ፓርቲው ይህን ተመልክቶ ፎቶዋቸው በጉራጌ ዞን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ለቅስቀሳ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ ያረጋገጠ ሲሆን፣ ስህተቱ የተፈጠረው የምርጫ ቅስቀሳዎች በምርጫ ወረዳ ደረጃ ተመርቶ የሚሠራ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

በፓርቲው ሕዝብ ግንኙነቱ አቶ ናትናኤል ፈለቀ በተጻፈው ደብዳቤ፣ ፓርቲው በይፋዊ ትስስር ገጾች ላይ ምስሉን አለመጠቀሙን ይገልጻል፡፡

ይህን ተከትሎም ፓርቲው የባለ መብቷን ምስል የተጠቀመባቸው ባነሮች እንዲወርዱ ለወረዳዎች ትእዛዝ ተላልፏል በማለት ለተፈጠረው መስተጓጎል ዛህራ መሐመድን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ነገር ግን ፎቶዬ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ውሏል ያሉት ዛህራ መሐመድ አሁንም ቢሆን ለቅስቀሳ የተሰቀሉት ፎቶዎች እንዳልወረዱ ገልጸዋል፡፡

ኢዜማ የቅስቀሳ ባነሮቹ እስካሁን ድረስ ለምን እንዳልወረዱ የሰጠው ተጨማሪ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img