Sunday, September 22, 2024
spot_img

በሳኡዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብት እንዲከበር ለመምከር ኢትዮጵያ ልኡክ ላከች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 12፣ 2013 ― በሳዑዲ ዐረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብት እንዲበር ለመምከር ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ኤጄንሲዎች የተውጣጣ ልኡክ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ልኡክ ቡድን ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብት የሚከበርበትንና በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሰላም የሚመለሱበትን መንገድ እንደሚያመቻች ነው የገለጸው፡፡

መግለጫው በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ውይይት ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑ ስደተኞችን በመመለስ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ይገመግማል ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዐረቢያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ወደ ሳኡዲ የመግባት ሙከራ ውቅያኖስ ውስጥ ከመስጠምና የሀውሲ ታጣቂዎች ጥቃት ሰለባ መሆንን ጨምሮ በርካታ አደጋዎች እንዳሉት ገልጿል፡፡

የሳዑዲ ዐረቢያ ድንበር ሰፊ በመሆኑ ስደተኞች ድንበር አልፈው መግባት አይሳካላቸውም፤ የስደተኖቹንም ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል፡፡

የሳዑዲ መንግሥት የድንበር የጸጥታ ህግን በሚጥሱ ላይ ቅጣት እንደሚጥልና ከድንበር አካባቢ ሰዎች የሚያዘዋውሩትንም እንደሚከለክል አስታውቋል፡፡

ከሰሞኑ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጽጥታ ኃይሎች ክፉኛ እየተዋከቡ እንዲሁም ለእስር ጭምር እየተዳረጉ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img